ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 12ኛውና ከፍተኛው የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ የሆነው ጣና ፎረም ከመጀመሩ አስቀድሞ የኬንያውን ምክትል ፕሬዝዳንት ኪቱሬ ኪንዲኪን ተቀብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኬንያውን ምክትል ፕሬዝዳንት በመቀበላቸው የተሰማቸውን ደስታ በማህበራዊ ሚዲያ ገጽ የገለጹ ሲሆን፤ በቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ አጭር የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን አስታውቀዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: