በቻይና የተሰራው እና ለጥልቅ የባሕር ውስጥ አሰሳ የሚያገለግለው መሳሪያ በደቡብ ቻይና ባሕር በ4 ሺ 140 ሜትር ጥልቀት ላይ የተሳካ ሙከራ አድርጓል።
በባሕር ውስጥ እስከ 6 ሺ ሜትር ድርስ ጠልቆ በመግባት ምስልን በፍጥነት የሚያስተላልፍ መሆኑን ዥንዋ ዘግቧል።
በሻንጋይ ጂያኦ ቶንግ ዩንቨርስቲ የተሰራው ይህ ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ካሜራዎች የተገጠመለት እና የሮቦቲክ ቴክኖሎጂን የያዘ መሆኑ ተነግሯል።
አዲሱ የቻይና ቴክኖሎጂ በጥልቅ የባሕር አካላት ላይ የሚካሄደውን ምርምር አንድ እርምጃ ወደ ፊት የሚያራምድ ነው ተብሎለታል።
በሃብተሚካኤል ክፍሉ
#EBC #ebcdotstream #China #Technology