የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እና የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በአሶሳ ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በአሶሳ ከተማ እየተገነባ ያለውን የአህመድ ናስር መታሰቢያ ስታዲየም የግንባታ ሂደትንም አመራሮቹ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
የስታዲየሙ ግንባታም በአጭር ጊዜ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ሊተባበር እንደሚገባ ሚኒስትሯ ገልጻል።
አመራሮቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትናንተናው ዕለት የተመረቀውን የአሶሳ ሕዳሴ ሙዚዬምን ጎብኝተዋል።
በአሶሳ ከተማ የተገነባውና የኮሪደር ልማቱ አካል የሆነውን አነስተኛ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳም ተመልክተዋል።
በጉብኝቶቹ ላይ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሳልሃዲን ሰዒድም ተገኝቷል።
የአሶሳ ስቴዲየም ግንባታ ከተጀመረ 11 ዓመት ሆኖታል።
በጀማል አህመድ
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #sports #infrastructure