የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እንዳስታወቁት ፕሬዚዳንት ፑቲን ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ሩሲያ በቱርኪዬ ኢስታንቡል የጀመረችውን ቀጥተኛ ድርድር ከዩክሬን ጋር ለመቀጠል ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
ላቭሮቭ አክለውም የሩሲያ እና የዩክሬን ልዑካን በኢስታንቡል ፊት ለፊት ተገናኝተው እንደሚወያዩም መግለጻቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
ሩሲያ እና ዩክሬን በቱርኪዬ ኢስታንቡል ከአንድ ወር በፊት የሰላም ድርድር አድርገው ነበር። ድርድሩ ያለበቂ ስምምነት መጠናቀቁ ይታወሳል።
ይሁንና የአሁኑ ውይይታቸው መቼ እንደሚደረግ ዘገባው በግልጽ ያለው ነገር የለም።