የሀገር መሠረታዊ ሕልውና፣ ሰላም እና ደኅንነት ከዘላቂ ጸጥታ እና ከጠንካራ ተቋማዊ ግንባታ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገራችንን ሉዓላዊነት እና የሕዝብ ሰላም ከማስጠበቅ ባሻገር፣ ወቅታዊ ተግዳሮቶችን በብቃት ለመመከት የሚያስችል ሁለገብ ዝግጁነት እያሳየ ይገኛል።
የሠራዊቱ ዘርፈ ብዙ አቅም የተገነባው በጥልቅ ተቋማዊ ሪፎርም፣ በዘመናዊ ትምህርት እና ሥልጠና፣ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ተመሥርቶ ነው።
ተቋሙ የሠራዊቱን መዋቅር ከዘመናዊ የውጊያ ስልቶች ጋር እያጣጣመ ሲሆን፣ ወታደራዊ ትምህርት ቤቶች እና ኮሌጆች ስትራቴጂያዊ አመራርን እና ታክቲካዊ ዕውቀትን በዘመናዊ መንገድ እንዲያስተምሩ ተደርገዋል።
የአስተዳደር፣ የሎጂስቲክስ እና የሰው ኃይል አያያዝም በዲጂታል ሥርዓቶች እና በግልጽነት መርሆዎች እንዲመሩ ተደርጓል።
ዘመናዊውን ጦር ሜዳ ፍላጎት ለማሟላትም የድሮን ቴክኖሎጂዎች፣ የራዳር እና የሳተላይት መረጃ መረቦች በመዋሃድ የክትትል አቅሙ ተጠናክሯል።
የመከላከያ ሠራዊቱ ጥንካሬ በመሣሪያ ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በአመራሩ ጥራት፣ በሙያዊ ዲሲፕሊን እና በሠራዊቱ የሞራል ጽናት ላይ የተመሠረተ ነው።
ከሕዝብ ጋር በቅርበት የሚሠራ፣ የሕግ የበላይነትን የሚያከብረው ሠራዊት፤ የምድር ኃይል፣ አየር ኃይል እና የድጋፍ ሰጪ ክፍሎች ተቀናጅተው በመንቀሳቀስ ከፍተኛ የማድረግ አቅም ፈጥረዋል።
የሠራዊቱ ዓላማ ሀገርን ከውጫዊ እና ውስጣዊ አደጋዎች መጠበቅ እና የዜጎችን ሰላም ማረጋገጥ ነው። ዛሬ የደረሰበት የዝግጁነት ደረጃ በተከናወኑ ተቋማዊ ጥንካሬዎች እና በሠራዊቱ አባላት መሥዋዕትነት የተገኘ ነው።
የድል እና የሰላም መሠረቱ ቀጣይነት ያለው ዝግጅት፣ የማይናወጥ ዲሲፕሊን እና ለሀገር ሉዓላዊነት የተሰጠ ጥልቅ የክብር ኃላፊነት ነው።
ሠራዊቱ ሁልጊዜም ለሀገሩ ሁለንተናዊ ደኅንነት እና ለሕዝቡ ሰላም በብቃት ለመቆም ዝግጁነቱ የጸና ነው።
በአድማሱ አራጋው
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: