Search

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ከሁዋዌ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤሪክ ዩዋን ጋር ተወያዩ

ቅዳሜ ጥቅምት 21, 2019 60

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ የሁዋዌ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን በቅርቡ ሥራ ከጀመሩት ኤሪክ ዩዋን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በውይይታቸው ወቅት መንግሥት የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ ለማስቀጠልና ለማፋጠን እየሠራቸው ያሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሥራዎች እጅግ አበረታች መሆናቸውን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸውልኛል ብለዋል።

ሁዋዌ የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይና ብሔራዊ የልማት ግቦቻችንን ለማሳካት በምናደርገው ጥረት ውስጥ፣ በተለይም በአይሲቲ መሠረተ ልማትና በግንኙነት ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ይገኛልም ነው ያሉት።

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ጉዞም ከሁዋዌ ጋር በትብብር፣ በብሔራዊ ባለቤትነት፣ በዘላቂነት፣ በደኅንነትና በአካባቢያዊ እሴት ፈጠራ መርሆዎች ላይ ተመሥርተን በምንሠራባቸው የትብብር መስኮች ዙሪያ መምከራቸውንም ገልጸዋል።

የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታችን በእመርታ እየተጓዘ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ሁዋዌም ለዚህ ዕድገት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ እና ያለንን የሥራ ግንኙነት አጠናክረን ለመቀጠል ተስማምተናል ብለዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: