Search

አዋሽ ባንክ 38.3 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ አስመዘገበ

ቅዳሜ ጥቅምት 21, 2019 60

አዋሽ ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት 38.3 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታውቋል።

የአዋሽ ባንክ ባለአክሲዮኖች 31ኛ መደበኛ እና 19ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥቅምት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ተካሂዷል።

በጉባኤውም የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጉሬ ኩምሳ የባንኩን ዓመታዊ ሪፖርት ለጉባኤው ያቀረቡ ሲሆን፣ አዋሽ ባንክ እስከ ፈረንጆቹ ሰኔ 30 ቀን 2026 ባለው ጊዜ ውስጥ አጠቃላይ ሀብቱ ከ624 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ገልጸዋል።

ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ181 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ወይም በ41 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የባንኩ አጠቃላይ የተከፈለ ካፒታል ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፣ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል በሂሳብ ዓመቱ ማጠናቀቂያ ላይ 38 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተመላክቷል።

የባንኩ አጠቃላይ ገቢም 84 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ከቀድሞው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ31 በመቶ ማደጉ በሪፖርቱ ላይ ተጠቁሟል።

በበጀት ዓመቱ ባንኩ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ክፍሎች የሰጠው የብድር መጠን 54 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር እድገት በማሳየት 274 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

በሳምሶን በላይ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: