የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ የዩክሬን 34ኛ ዓመት የነጻነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በዩክሬን በተገኙበት ወቅት 1.46 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ወታደራዊ እርዳታ ለዩክሬን እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።
አጠቃላይ እርዳታው ወታደራዊ መሳሪያዎች እና የህክምና ቁሳቁሶችን ጨምሮ የተለያዩ ጥቅሎችን የያዘ ነው ተብሏል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለውም በዩክሬን እና ካናዳ ኢንዱስትሪዎች መካከል የጋራ ትብብርን ይመሰረታል ብለዋል።
ይህም ዩክሬንን በወታደራዊ መሳሪያዎች ማምረት ላይ ያላትን አቅም የሚጨምር ይሆናል ነው የተባለው።
ካናዳ የዩክሬን ዋንኛ አጋር ሀገር ስትሆን፤ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ጦርነት ከጀመረች ወዲህ ካናዳ ወደ 22 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እርዳታ ሰጥታለች ሲል የዘገበው አናዶሉ ነው።
በሀ/ሚካኤል ክፍሉ