Search

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በግንባር ቀደምትነት ተሰልፏል፡- ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)

ረቡዕ ጥቅምት 25, 2019 75

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከፍ ያለ ዕድገት በማስመዝገብ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በግንባር ቀደምትነት መሰለፉን የገንዘብ ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ።

በሀገራችን የኢኮኖሚ ታሪክ ትልቅ ምዕራፍ የሆነው የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ወቅታዊ የማድረግ ሥራ (GDP Rebasing) ውጤት ይፋ ሆኗል።

ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፣ የ2017 በጀት ዓመት የሀገራችን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ወደ 24.03 ትርሊዮን ብር (201.42 ቢሊዮን ዶላር) ከፍ ማለቱን ገልጸዋል።

በ2018 በጀት ዓመት በተመዘገበው ዕድገት ደግሞ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 31.86 ትርሊዮን ብር (210.7 ቢሊዮን ዶላር) ደርሷል ያሉት ሚኒስትሯ፣ በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት 3ኛው ትልቅ ኢኮኖሚ መሆኗ ተረጋግጧል ብለዋል።

ይህ አዲስ ስሌት የዲጂታል ፋይናንስ፣ የኢንዱስትሪ፣ የማዕድን እና የዘመናዊ ግብርና ዕድገቶችን በግልጽ የሚያሳይ ሲሆን፣ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የተከናወነና ሙሉ በሙሉ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን (SNA 2008) የጠበቀ እንደሆነ መግለጻቸውን ከብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: