ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር መወያየታቸውን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ “በአህጉራዊ አስተዳደር፣ አካታች የፖለቲካ ሂደቶች፣ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ የልማት ጉዳዮች እንዲሁም የአፍሪካን አመራር በማጠናከር ዙሪያ ሰፊ የሃሳብ ልውውጥ አድርገናል” ብለዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: