Search

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 584 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሰኞ ጥቅምት 30, 2019 101

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 364 ኢትዮጵያውያን በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 7 ዙር በረራ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከተመላሾቹ መካከል 1 ሺህ 432 ወንዶች፣ 131 ሴቶች እና 21 ሕፃናት ሲሆኑ፣ 25ቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ አዳጊዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያ እና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራም እየተሠራ መሆኑን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

 

መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ114 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: