በሴኔጋል መዲና ዳካር እየተካሄደ በሚገኘው 4ኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ መድረክ፣ ኢትዮጵያ በውድድሩ ሁለተኛ የወርቅ ሜዳልያዋን አግኝታለች።
በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ሀገሩን ወክሎ የተካፈለው አትሌት ዋቢ ወጂራ፣ ርቀቱን በ3 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ73 ማይክሮ ሴኮንድ ቀዳሚ ሆኖ በማጠናቀቅ ድል ተቀዳጅቷል።
ይህ ድል ለኢትዮጵያ በውድድር መድረኩ የተመዘገበ ሁለተኛው የወርቅ ሜዳልያ ሲሆን፤ አስቀድሞ በወንዶች 2 ሺህ ሜትር መሰናክል ሩጫ አትሌት ጁነዲን አብዶ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ለሀገሩ አስገኝቷል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: