በሐረር ከተማ በግብርና ኢንቨስትመንት የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገሩ መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለጹት፣ በአነስተኛ መነሻ ካፒታል የተጀመሩ ኢንቨስትመንቶችን በጥቂት ዓመታት ውስጥ የካፒታል አቅማቸውን ማሳደግ ተችሏል።
የድለባ ጊዜያቸውን የጨረሱ የሐረር ሠንጋዎችን፣ በየሦስት ወሩ ለውጭ ገበያ በማቅረብም የውጭ ምንዛሪ ግኝት እንዲጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።
በቀጣይም በዚህ ዘርፍ በሰፊው በመሰማራት የሀገራችንን ኢኮኖሚ እና የውጭ ምንዛሪን ለማሳደግ በሚደረገው ሂደት ውስጥ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለደርሻ አካላት በትጋት ሊሰሩ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: