Search

አትሌት ነጻነት ሰሎሞን ለኢትዮጵያ 3ኛውን የወርቅ ሜዳልያ አስመዘገበች

ሰኞ ጥቅምት 30, 2019 202

በሴኔጋል ዳካር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 4ኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ መድረክ፣ ኢትዮጵያ ሦስተኛ የወርቅ ሜዳልያዋን በሴቶች 800 ሜትር ማግኘት ችላለች።

በውድድሩ ጠንካራ ፉክክር ያደረገችው አትሌት ነጻነት ሰሎሞን፣ ርቀቱን በ2 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ ከ44 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ቀዳሚ በመሆን ለሀገሯ የወርቅ ሜዳልያ አስገኝታለች።

 

ከዚህ ድል አስቀድሞ በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር አትሌት ዋቢ ወጂራ እንዲሁም በወንዶች 2 ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ጁነዲን አብዶ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ ማስመዝገባቸው ይታወሳል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: