Search

የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል መሪነት እና የCOP32 ታሪካዊ ኃላፊነት

ረቡዕ ኅዳር 02, 2019 146

የኢንዱስትሪ አብዮት የፈጠረው የዘመነ ቴክኖሎጂ ለሰው ልጅ ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ ቢኖረውም የዕድገቱ መሠረት የሆኑት የኃይል ምንጮች ለአየር ንብረት መዛባት ዋነኛ መንስኤ ሆነዋል።

ግዙፎቹ ኢንዱስትሪዎች፣ የአምራች ዘርፎች እና የትራንስፖርት መዋቅሮች ይጠቀሙበት የነበረው የድንጋይ ከሰል፣ ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ከፍተኛ መጠን ያለው የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት ወደ ከባቢ አየር በመልቀቅ የዓለምን ሙቀት እጅግ ከፍ አድርጎታል።

 

ይህ ያልተገደበ የነዳጅ አጠቃቀም የካርቦን ልቀቱን በማባባስ ድርቅን እና የጎርፍ አደጋዎችን በማስከተል የሰው ልጅ ሕልውናን ሥጋት ውስጥ ከትቷል።

ይህንን ዓለም አቀፋዊ ውድመት ለመግታት እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ከካርቦን ልቀት ነፃ ለማድረግ የታዳሽ ኃይል አጠቃቀም ብቸኛው ዘላቂ መፍትሔ ሆኗል።

በዚህም መሠረት የዓለም መንግሥታት ከነዳጅ ምንጮች ፊታቸውን በማዞር ወደ ውኃ፣ ንፋስ፣ ጂኦተርማል እና የፀሐይ ኃይል ልማት በስፋት እየተሸጋገሩ ይገኛሉ።

በዚህ ዓለም አቀፍ የኢነርጂ ሽግግር ውስጥ ኢትዮጵያ በተግባር የተደገፈ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች ትገኛለች።

ከተፈጥሮ ባገኘችው እምቅ ሀብት በመጠቀም የምታመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል 98 በመቶ የሚሆነው ሙሉ በሙሉ ከንጹህ እና ታዳሽ ምንጮች የተገኘ ነው።

 

ከጠቅላላው ከ9 ሺህ 750 ሜጋ ዋት በላይ ከደረሰው የማመንጨት አቅም ውስጥ 94 በመቶው ከውኃ ኃይል የሚመነጭ ሲሆን፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዚህ አረንጓዴ ቁርጠኝነት ትልቁ ማረጋገጫ ነው።

በተጨማሪ እንደ አዳማ፣ አሸጎዳ፣ አሰላ እና አይሻ ሁለት ያሉ የንፋስ ኃይል ጣቢያዎች የኃይል ስብጥሩን እያጎለበቱት ይገኛሉ።

 

በቀን 24 ሰዓት ሙሉ ቋሚ ኃይል መስጠት የሚችለው የስምጥ ሸለቆ የጂኦተርማል ሀብት እና የፀሐይ ብርሃን አጠቃቀም ኢትዮጵያን የምሥራቅ አፍሪካ ንጹሕ የኃይል ማዕከል አድርጓታል።

በቀን 24 ሰዓት ሙሉ ቋሚ ኃይል መስጠት የሚችለው የስምጥ ሸለቆ የጂኦተርማል ሀብት እና የፀሐይ ብርሃን አጠቃቀም ኢትዮጵያን የምሥራቅ አፍሪካ ንጹሕ የኃይል ማዕከል አድርጓታል።

ኢትዮጵያ ይህንን እምቅ አቅም ወደ ሥራ በማስገባት ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል የምታደርገው ጥረት በኃይል ማመንጨት ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም።

 

በ2016 ዓ.ም በነዳጅ የሚሠሩ የቤት መኪኖችን ማስገባት ማገዷ እና በ2017 ዓ.ም የቤት እና ከባድ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አስመጥታ በመገጣጠም አርዓያነቷን አስመስክራለች።

ይህም ከውስጥ ከሚመነጨው ርካሽ የውኃ ኤሌክትሪክ በመጠቀም የነዳጅ ወጪን ከመቀነሱም በላይ የካርቦን ልቀትን በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።

 

እስከ 2030 ድረስ 65 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተያዘው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከካርቦን ነፃ የትራንስፖርት ፖሊሲዎች እና ለጎረቤት ሀገራት የሚደረገው የኃይል ኤክስፖርት ለአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ዘላቂ ልማት ያላትን ተጨባጭ አቋም ያሳያሉ።

እስከ 2030 ድረስ 65 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተያዘው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከካርቦን ነፃ የትራንስፖርት ፖሊሲዎች እና ለጎረቤት ሀገራት የሚደረገው የኃይል ኤክስፖርት ለአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ዘላቂ ልማት ያላትን ተጨባጭ አቋም ያሳያሉ።

ይህ የላቀ ሀገራዊ ተሞክሮ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ ግንባር ቀደም አድርጓታል።

በዚሁ መሠረት እ.ኤ.አ በ2027 አዲስ አበባ 32ኛውን የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ (COP32) በይፋ ታስተናግዳለች።

ከ80 ሺህ በላይ የዓለም መሪዎች፣ ተደራዳሪዎች እና ባለሙያዎች በሚታደሙበት በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ኢትዮጵያ አዘጋጅ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካን እና የታዳጊ ሀገራትን ድምፅ በማስተጋባት ረገድ የላቀ ኃላፊነት ትወጣለች።

በጉባኤው የፋይናንስ ቃል ኪዳኖች ለተጋላጭ ማኅበረሰቦች በቀጥታ የሚደርሱበት አሠራር እንዲሰፍን በዓመት 50 ቢሊዮን ዶላር የሚያቀናጀውን የአፍሪካ አየር ንብረት ፈንድ በማጠናከር እና የታዳሽ ኃይል ተሞክሮዋን ለዓለም በማካፈል ረገድ ትልቅ አህጉራዊ አደራ አለባት።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ፕሬዝዳንትነት የሚመራው ይህ ጉባኤ ኢትዮጵያ በተግባር ያረጋገጠችውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ እውነታ ለዓለም ሕዝብ የምታሳይበት እና ዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ፍትሕ የምታጎለብትበት ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ ይሆናል።

በለሚ ታደሰ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: