Search

ኢትዮጵያ እና ኤዥያ ኢንፍራስትራክቸር ኢንቨስትመንት ባንክ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተወያዩ

ረቡዕ ኅዳር 02, 2019 84

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከኤዥያ ኢንፍራስትራክቸር ኢንቨስትመንት ባንክ (AIIB) ፕሬዝደንት ዞ ጂያይ ጋር የአጋርነት ሥራዎችን ለማስቀጠል ያለመ ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ወቅት ቀደም ሲል ተጀምሮ የነበረውን የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ፋይናንስ የማድረግ ሂደት አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ የረጅም ጊዜ አብሮ የመሥራት ዕድሎችን ለመፍጠር እና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክቶችን ለመቅረፅ የሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ መክረዋል።

በተጨማሪም ኤዥያ ኢንፍራስትራክቸር ኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በሚካሄደው የCOP32 ጉባኤ ላይ የሚኖረውን የድጋፍ እና የተሳትፎ ሁኔታ በተመለከተ ይመካከሩ ተደርጓል።

 

የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: