ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርጉት ድጋፍ እና የሚገቡት የፋይናንስ ቃል ኪዳን ግልጽ፣ አስቀድሞ የሚታወቅ እና ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ መሆን እንዳለበት አሳሰቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር የፋይናንስ ድጋፎች "ምን ያህል? እስከ መቼ? በምን ዓይነት መመዘኛ?" ለሚሉት ሦስት ዋና ጥያቄዎች ግልጽ ምላሽ መስጠት አለባቸው ብለዋል።
ይህ ሲሆን ብቻ ሀገራት በቂ በጀት ለመመደብ፣ ኢንቨስተሮች ለመወሰን እና ማኅበረሰቡ አስቀድሞ ለመዘጋጀት እንደሚያስችለው ገልጸዋል።
ታዳጊ ሀገራት የሚከፍሉት አሰቃቂ የቢሊዮን ዶላሮች ወለድ ለአየር ንብረት ለውጥ የመቋቋም አቅማቸውን እየጎዳው መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የብድር ውሳኔዎቻቸውን ማሻሻል እንዳለባቸው እና የበካይ ጋዝ ልቀት በፍጥነት እንዲቀንስ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ ቀጣዩን 32ኛውን የጉባኤ መድረክ በምታዘጋጅበት ወቅት እነዚህን አስቀድሞ የመሥራት እና ፈጣን ምላሽ የመስጠት የፋይናንስ ስልቶችን ማዕከል እንደምታደርግ አስታውቀዋል።
በለሚ ታደሰ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: