የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በUNFCCC ስር የአረብ ቡድን አባል ሀገራት የልዑካን መሪዎች ስብሰባ ላይ ተጋብዘው ንግግር አድርገዋል።
አባላቱ በስብሰባው ወቅት፣ በኢትዮጵያ አመራር እና በCOP32 ሂደት ላይ የተመራጭ ፕሬዚዳንቱ በሚያሳዩት መሪነት ላይ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያና በአረብ ቡድን አባል ሀገራት መካከል ያለውን የቆየና ጠንካራ ግንኙነት አንስተዋል።
ተመራጭ ፕሬዚዳንቱም ኢትዮጵያ ከሁሉም ተዋዋይ አካላት ጋር በቅርበት በመሥራት የተሳካ COP32 ለማካሄድ ያላትን ቁርጠኝነትና ዝግጁነት ለቡድኑ ማረጋገጣቸውን ከኮፕ32 ኢትዮጵያ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: