-👉በኢትዮጵያ የአየር ንብረት እርምጃ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው።
👉 የኤል ኒኞ (El Niño) ክስተት ተመልሶ ሲመጣ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ከማኅበረሰቡና ከአካባቢ አስተዳደሮች ጋር በጋራ እየሠራን ነው።
👉 የአየር ንብረታችን ከድንበራችንም ባሻገር ትልቅ ፋይዳ አለው፤ ለጎረቤት ሀገራት የምናቀርበውን ኃይል ጨምሮ፣ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው የኤሌክትሪክ ኃይላችን የሚመነጨው ከውኃ ነው።
👉 ኢትዮጵያ ለዓለም የአረቢካ ቡናን አበርክታለች።
👉 ለአየር ንብረት ለውጥ የምንሰጠው ምላሽ በ“መደመር” ፍልስፍናችን የሚመራ ነው። ፍልስፍናው ሕዝብን፣ ተቋማትን እና ሀብትን በአንድ የጋራ ዓላማ ዙሪያ ያሰባስባል።
👉 በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በችግኝ ተከላ ይሳተፋሉ፤ በጋራ በመሆን ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን የተከልን ሲሆን፣ የተራቆቱ መሬቶችን መልሰን እያለማንና ደኖቻችንን እያሰፋን እንገኛለን።
👉 የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሥራ ዕድሎችን ፈጥሯል፤ የዜጎችንም ኑሮ አሻሽሏል። ዛሬ ችግኝ መትከል የቤተሰብ ልምድ ሆኗል።
👉 ከተሞቻችን በማስፋት የጎርፍ መከላከያዎችን እየገነባን፣ የተበከሉ ወንዞችን እያጸዳን እንዲሁም የወንዝ ዳርቻዎችን ቤተሰቦች ወደሚሰባሰቡባቸውና ሕፃናት ወደሚጫወቱባቸው መናፈሻዎችና የእግረኛ መንገዶች እየቀየርን ነው።
👉 በኃይል አቅርቦታችን ረገድ የረጅም ጊዜ እይታን በመከተል የንፋስ፣ የፀሐይና የእንፋሎት (ጂኦተርማል) ኃይልን እያለማን ነው።
👉 ዝናብ አጠር ዓመት በኢኮኖሚያችን ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የኒውክሌር ኃይልን ለማልማት አቅደን እየሠራን ነው።
👉 መሬታችንን ለመከታተል የሳተላይት መረጃን የምንጠቀም ሲሆን፣ ለአርሶ አደሮች ቀድሞ ማስጠንቀቂያ ለመስጠትም ትንበያዎችን በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እያሻሻልን እንገኛለን።
👉 “ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያችን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ቤተሰቦች ተደራሽ ለማድረግ ያግዘናል።
👉 በሀገራት መካከል ያለው ፉክክር እያደገ ቢመጣም እንኳ፣ አስተማማኝ የፋይናንስ አቅርቦት ትብብርን ይጠይቃል።
👉 ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን (COP32) ታስተናግዳለች። ቅድመ እርምጃንም የጉባኤው ማዕከል እናደርጋለን።
በአድማሱ አራጋው
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: