በሀገር አቀፍ ደረጃ 1.5 ሚሊየን ቤቶችን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት፤ ለግንባታው የሚያስፈልጉት ፋይናንስ፣ የኮንስትራክሽን ግብአቶች እንዲሁም የሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን ማሳደግ ቀድሞ የታሰበበት ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ቤቶች ሲገነቡ የፋይናንስ ዘርፉ አብሮ ሊሠራ እንደሚገባ፣ ዜጎች ቤቱን በቀላሉ ተረድተው በባንኮች ሞርጌጅ አማካኝነት እየኖሩበት በሂደት የሚከፍሉበት አሠራር መዘርጋቱን አንስተዋል።
ሥራውን በብቃት ለማፋጠን በመንግሥት እና በግል አጋርነት በመሥራት በአዲስ አበባ ከዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከመቶ ሺህ በላይ ቤቶች ተጀምረው አብዛኛዎቹ በጥሩ ሁኔታ መጠናቀቃቸውን ጠቅሰዋል።
በከተሞችም ሆነ በገጠር ደረጃ የመጸዳጃ፣ የውኃ፣ የመብራት እና ተስማሚ የመኖሪያ ቤት እጥረት ሰፊ በመሆኑ ሥራው አግሬሲቭ በሆነ እና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ መከናወን እንዳለበት አሳስበዋል።
የሚሠራው ሥራ አንዲትን ደሃ እናት ሕይወት ጨምሮ የእያንዳንዱን ዜጋ የኑሮ ደረጃ ማሻሻል የሚገባው መሆኑ፤ ልማቱ የሀብት ፍሰትን በማስተካከል የሁሉንም ሕይወት የሚቀይር መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።
ጅምሮቹ ጥሩ እና ፈጣን ቢሆኑም አሁን ካሉት ክፍተቶች በመማር ተጨማሪ ጥረት በማድረግ እና በጋራ በመበርታት ከተሞቻችንን፣ የዜጎቻችንን የሕይወት ዘዬ እና የኑሮ ደረጃ አጠናክሮ መቀየር ቀጣዩ ዋና ሥራ መሆኑን ጠቁመዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: