Search

ዋሽንግተንን ለማስዋብ 2 ቢሊዮን ዶላር የጠየቁት ፕሬዚዳንት ትራምፕ

ሰኞ ነሐሴ 19, 2017 44

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋና ከተማዋን ዋሽንግተንን ለማስዋብ 2 ቢሊዮን ዶላር በጀት እንደሚያስፈልጋቸው ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱ ዋሽንግተንን ንፁህ እና ውብ ለማድረግ ያስችላል ላሉት የከተማ ማስዋብ እቅድ ለአሜሪካ ኮንግረስ የ2 ቢሊዮን ዶላር የበጀት ጥያቄ እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል።

ትራምፕ ይህን እቅድ ይፋ ባደረጉበት ወቅት፥ አሁን ያሉት የከተማዋ መብራቶች በአብዛኛው ያረጁና የተሰበሩ ናቸው ብለዋል።

መንገዶቹ ተበላሽተዋል፣ ፓርኮቹ አረንጓዴና ዓይን የሚስቡ አይደሉም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ አዲሱ እቅድ ይህን እንደሚያስተካክል፣ ከተማዋን ውብ፣ ፅዱና ሰላማዊ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ትራምፕ ዋሽንግተንን  ከመቼውም የበለጠ ሰላማዊ፣ እንከን የለሽ እና ውብ ገፅታን የተላበሰች ያደርጋታል ያሉት እቅዳቸው የከተማዋ መንገዶች እድሳት፣ በፋውንቴን የተዋበ የህዝብ ፓርክ ግንባታ፣ የመንገድ መብራቶችን በአዲስ መቀየር፣ የከተማዋ መለያ የሆኑ ሐውልቶችን ማደስ እና ማፅዳትን ያካተተ እንደሆነ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ዋሽንግተን ዲሲን ለማደስ እና ለማስዋብ ያወጡት ይህ እቅድ ከዋና ከተማዋ በ4.8 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ያለውን አካባቢ የሚያካልል ሲሆን ትግበራውም በ12 ወራት እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።

በዋሲሁን ተስፋዬ

#Washington #Trump #Corridor #USA