የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሺጌሩ ኢሺባ ሀገራቸው ሕንድ ውቅያኖስን ከአፍሪካ ጋር የሚያገኝ አዲስ የኢኮኖሚ ዞን ለመመስረት እንደምትፈልግ ሀሳብ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በጃፓን በተካሄደው ዓለም አቀፉ የአፍሪካ ልማት ኮንፈረንስ ላይ ሀገራቸው የሕንድ ውቅያኖስ አካባቢ ከአፍሪካ አህጉር ጋር በማገናኘት የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብሯን ለማሳደግ እንደምትሠራ ተናግረዋል።
ጃፓን ከ30 ሺህ በላይ አፍሪካውያን ባለሙያዎችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በማሰልጠን ዲጂታል አሠራርን ለመፍጠር እና የአፍሪካ ልማት ባንክን ለመደገፍ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ገልጻለች።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#Japan #Africa #Indianocean