የፍትሕ ሥርዓቱን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት የፍትሕ አካላት ለሰጡት ፍርድ ተጠያቂ የሚሆኑበት አሠራርም ሊዘረጋ ይገባል ሲሉ የሕግ ባለሙያው አቶ አባይ መርጋ ገለፁ።
ከለውጡ ማግስት ፍትህ አሰጣጥን የማፋጠን፣ ኢ-ፍትሐዊ አዋጅን ማሻሻል፣ ባህላዊው የፍትህ ስርዓት ዘመናዊውን የፍትህ ስርዓት እንዲያግዝ የማድረግ የሪፎርም ሥራ መከናወኑን ከኤፍ.ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ አስታውሰዋል።
ሆኖም በፍትህ አሰጣጥ ረገድ ካለመቀናጀት የተነሳ ተደጋጋሚ ቀጠሮ በመስጠት የሚፈጠር የጊዜ መራዘም፣ ካለ በቂ ማስረጃ ውሳኔ ማሳለፍ እና የተከሳሽን ሕገ-መንግስታዊ መብት የሚነኩ ድርጊቶች እንደሚስተዋሉ ጠቁመዋል።
ይህን ክፍተት ለመድፈን የፍትህ ስርዓቱ ገለልተኛ እና የተቀናጀ፤ የወንጀል ምርመራው በመረጃ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ህብረተሰቡም ወንጀልን በመከላከል ረገድ ከፍትህ አካላት ጋር መተባበር እንዳለበት ነው ያመላከቱት።
በአፎሚያ ክበበው
#Justice #Reform #Accountability