Search

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞች ብዛት ከ50 ሚሊዮን በላይ በማድረስ በአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃን ያዘ

ሓሙስ ኅዳር 10, 2019 106

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ50.2 ሚሊዮን ደንበኞች በአፍሪካ ሁለተኛው ግዙፍ የደንበኞች መሠረት ያለው ባንክ መሆኑን አስታውቋል።

60 ሚሊዮን ደንበኞች እንዳሉት የተመላከተው የናይጀሪያው አክሰስ ባንክ  ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ50.2 ሚሊዮን ደንበኞች ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ከስምንት አሥርተ ዓመታት በላይ የሀገራችን የምጣኔ ሀብት ዋልታ ሆኖ የቆየው ባንኩ፣ ከከተማ እስከ ገጠር በዘረጋው ሰፊ የቅርንጫፍ እና የአገልግሎት አድማስ እንዲሁም በየጊዜው በሚያስተዋውቃቸው ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፉ አሠራሮች እና አገልግሎቶች በደንበኞች ዘንድ ተመራጭነትን ማትረፍ መቻሉን ገልጿል።

ባንኩ መርጠውት እና ተማምነውት አብረውት ለሚሠሩ ደንበኞቹ ምስጋና አቅርቧል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: