Search

"የኒውክሌር ጦርነት አሸናፊ የለውም፤ ፈጽሞም መካሄድ የለበትም" - የሦስቱ መሪዎች ታሪካዊ መግለጫ

ሓሙስ ኅዳር 10, 2019 119

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ባካሄዱት ታሪካዊ የሦስትዮሽ ውይይት ማጠቃለያ ላይ የጋራ የሰላም መግለጫ አውጥተዋል።

የሦስቱ ልዕለ-ኃያላን ሀገራት መሪዎች በደቡብ ምሥራቅ ቻይናዋ ሼንዠን ከተማ እየተካሄደ ከሚገኘው የእስያ-ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር (APEC) ጉባኤ ጎን ለጎን ለ90 ደቂቃዎች ያህል ዝግ ውይይት አድርገዋል።

መሪዎቹ ከዚህ ቀደም የሁለትዮሽ ውይይቶችን ያደረጉ ቢሆንም፣ ሦስቱም በአንድ መድረክ ተገናኝተው የሦስትዮሽ ምክክር ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው።

መሪዎቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ "የኒውክሌር ጦርነት አሸናፊ የለውም፤ ፈጽሞም መካሄድ የለበትም" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ሀገራቱ የዓለምን የነዳጅ ምርትና አቅርቦት ለማሳደግ መወጠናቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመመለስ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ለማሻሻል ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የመሪዎቹ መግለጫ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ያለመከሰስ መብት ጉዳይም ያነሳ ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) እና ሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት ሥልጣናቸውን ከተገቢው ውጭ መጠቀም እንደሌለባቸው መስማማታቸውን አስታውቋል።

ይሁን እንጂ በመድረኩ ከተንጸባረቀው ዲፕሎማሲያዊ መቀራረብ ባሻገር፣ ሦስቱ መሪዎች ለዚህ ታሪካዊ ውይይት የተለያዩ ፍላጎቶችና ስትራቴጂካዊ ግቦችን ይዘው መቅረባቸው ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።

ፑቲን ከታሪካዊው የሶስትዮሽ ውይይት በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ ከሺ ጂንፒንግ እና ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ያደረጉትን የመጀመሪያቸው የሦስትዮሽ ውይይት "በዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ አዲስ ገጽ ነው" ሲሉ ገልጸውታል፡፡

ሦስቱ መሪዎች በተለያዩ ወሳኛ ጉዳዮች ላይ በነፃነትና በግልጽ መነጋገራቸውንም ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናግረዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: