Search

የልማት ትልቁ ትርጉም በዜጎች ዕለታዊ ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሓሙስ ኅዳር 10, 2019 84

የልማት ትልቁ ትርጉም በዜጎች ዕለታዊ ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ ትናንት ያስመረቅነው የኮሪደር ልማት የከተማችንን መሠረተ ልማቶች በማገናኘትና የመንገድ ኔትወርካችንን በማስፋት ከተማችንን የበለጠ ምቹና ለኑሮ ተስማሚ ከማድረጉም በላይ ለዜጎች ቀጥተኛ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ጥቅም አስገኝቷል ብለዋል።

ከ3 ሺህ 118 በላይ ሱቆች ታድሰውና አዳዲስ ተገንብተው፣ ከ491 በላይ የመኖሪያ ሕንፃዎችም ታድሰዋል ነው ያሉት ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።

ይህም ለነጋዴዎች የተሻለ የንግድ አካባቢና የገቢ ዕድል፣ ለሥራ ፈላጊዎች ከፍተኛ የሥራ ዕድል፣ ለነዋሪዎች ደግሞ የተሻለ የመኖሪያ አካባቢ፣ ምቹ የእንቅስቃሴ ሁኔታና የተሻለ የኑሮ ጥራት መፍጠሩን ገልጸዋል።

ለዚህ ውጤት መመዝገብ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ሥራውን ያስተባበራችሁ የከተማው አመራሮችና ሠራተኞች፣ ከጉልበት ሠራተኞች እስከ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎችና ሌሎች ተሳታፊዎች ላደረጋችሁት ትጋትና አስተዋፅኦ ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: