የአሜሪካው ግዙፉ የአቪዬሽን ኩባንያ ቦይንግ እና ኮሪያን ኤር 103 አውሮፕላኖችን ለመግዛት የ36 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት መፈራረማቸውን አስታውቀዋል።
ይህ ስምምነት 50 ቦይንግ 737-10 የመንገደኞች አውሮፕላኖችን እና 45 የረጅም ርቀት ጄቶችን ያካትታል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ኮሪያን ኤር በተጨማሪም ስምንት 777-8 የጭነት አውሮፕላኖችን እንደሚገዛ የሁለቱ ኩባንያዎች የጋራ መግለጫ አመልክቷል።
ስምምነቱ ይፋ የሆነው በደቡብ ኮሪያ እና በአሜሪካ የመንግስት ተወካዮች እና የንግድ መሪዎች መካከል በተደረገ ስብሰባ ላይ ነው።
የኮሪያ አየር መንገድ አዲስ የተፈራረመው ስምምነት የአውሮፕላን ቁጥሮቹን በእጥፍ እንደሚያሳድገው ተመላክቷል።