ሀገር አቀፍ የመንገድ ዘርፍ 2ኛ ጉባዔ በጅግጅጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በወቅቱ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ፤ መንግሥት መንገድን ከተሽከርካሪ ባሻገር ለእግረኛ እና ለሞተር አልባ ተሽከርካሪዎች ምቹ እንዲሆን በማሰብ ዘመናዊ የኮሪደር ልማትን በመገንባቱ ለውጥ አምጥቷል ብለዋል።
ከለውጡ ወዲህ የሶማሊ ክልል በመንገድ ዘርፍ ተጠቃሚ መሆን ከቻሉ ክልሎች መካከል ተጠቃሽ ሆኗል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ፕሮጀክቶችን በተቀናጀ መልኩ በመምራት የሕብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደተቻለን ተናግረዋል።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው፤ በ2017 በጀት ዓመት በፌደራል ደረጃ ከ101 ቢሊዮን ብር በላይ በመመደብ ከ1 ሺህ ኪሜ በላይ የመንገድ ግንባታ እና እድሳት መደረጉን አስታውሰዋል።
በዘርፉ የተሰራው ሥራ በቁጥር ብቻ ሳይሆን በጥራትም ተጠቃሽ መሆኑን የኮሪደር ልማቱ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።
በመድረኩ የሶማሊ ክልለ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ዑመር እንዲሁም የተለያዩ የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ