የመደመር መንግሥት በዕውቀት እና በክህሎት የዳበረ ዜጋን ለመፍጠር አሻጋሪ ዕቅዶችን ነድፎ እየተገበረ እንደሚገኝ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
3ኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ትምህርት ጉባኤ “በትምህርት የጸናች ሀገር፣ በጽናት የቆመ ትውልድ” በሚል መሪ ሐሳብ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በጉባዔው የተገኙት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጥራት ማስጠቂያ ፖኬጆች ትግበራ የተመዘገቡ ለውጦች ወጥነት እንዲኖራቸው በየደረጃው የክትትል እና ድጋፍ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ አብራርተዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ ፍቅሬ አማን በበኩላቸው በከልሉ ሁሉም የትምህርት እርከኖች የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሕብረተሰቡን ተሳትፎ የማጎልበት እና ተገቢ ድጋፎችን ተደራሽ የማድረግ ሥራዎች ትኩረት ይሰጣቸዋል ብለዋል።
በተቋማት የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ከትምህርቱ ዘርፍ ለሀገር ብልጽግና የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ አስፈላጊው ሁሉ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዝመራው አንደሞ በክልላዊ እና ሀገር አቀፍ የፈተና ሂደቶች የተመዘገቡ ጅምር ውጤቶችን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የተቀናጀ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የተገኙ ውጤቶች ሕብረተሰቡ ለዘርፉ ባለቤት ሆኖ እንዲሳተፍ አጋዥ መሆኑን አመላክተዋል።
ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ክልላዊ የትምህርት ጉባኤ የአፈጻጸም ግምገማዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ በዘርፉ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማት፣ ግለሰቦች እና ላቅ ያለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ይሰጣቸዋል።
በሰለሞን ባረና
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: