Search

የሩሲያ የመድኃኒት አምራቾች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

ረቡዕ ኅዳር 16, 2019 25

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና ጉባኤ (CPHIA 2026) ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የሩሲያ ልዑካን ቡድን ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ወቅት ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ ጤና ሚኒስቴር በሰው ኃይል ልማት ላይ ከሩሲያ ጋር በትብብር ለመሥራት እና ያሉትን ትብብሮች ይበልጥ ለማስፋፋት ፍላጎት እንዳለው ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል።

በተለይም የላቁ የሕክምና አገልግሎቶችን እና በጤናው ዘርፍ የተገኙ የቅርብ ጊዜ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት በቅንጅት መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የሩሲያ የፋርማሲዩቲካል እና የሕክምና መሣሪያ አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።

የሩሲያን ልዑካን ቡድን የመሩት የሩሲያ ፌዴሬሽን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ኦሌግ ሳላጋይ በበኩላቸው፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ጠንካራ ግንኙነት መመሥረቱን ገልጸዋል።

5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና ጉባኤ በአደረጃጀትም ሆነ በይዘት እጅግ የተሳካ ክንውን መሆኑን መስክረዋል።

በመድረኩ ላይ የታሪካዊው ባልቻ ሆስፒታል ዕድሳትን በተመለከተ መወያየታቸውን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ ይህም የሁለቱ ሀገራት የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ተጨባጭ ማሳያ መሆኑን አመልክተዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: