የኢፌዴሪ አየር ኃይል ያዘጋጀው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ “አየር ኃይላችን መመኪያችን” በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል።
በውድድሩ በወንዶች አትሌት ቢኒያም መላክ ሲያሸንፍ፤ በሴቶች አትሌት አዳኑ ኔንቆ ማሸነፍ ችላለች።
በወንዶች ውድድር አትሌት ሙቢን ሀጂ 2ኛ ሲወጣ፣ አትሌት ጭምዴሳ ደበሌ 3ኛ በመውጣት አጠናቅቀዋል።
በሴቶች ደግሞ አትሌት ቢቂሌ አምበሴ 2ኛ፣ አትሌት ቤቴልሄም ኦላና 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቅ ችለዋል።
በሩጫ ውድድሩ አንደኛ የወጡት እያንዳንዳቸው 500 ሺህ ብር ሽልማት እንዲሁም 250 ሺህ እና 150 ሺህ እንደየደረጃው 2ኛ እና 3ኛ ለወጡት ተበርክቶላቸዋል።
በምርጥ አሰልጣኞች በወንዶች ሁሴን ሼቦ ከሸገር ሲቲ፣ በሴቶች ተስፋዬ ነዳሳ ከሸገር ሲቲ ተሸልመዋል።
አሸናፊ አትሌቶች የሀገር አለኝታ በሆነው የአየር ኃይል የጎዳና ላይ ሩጫ በመሳተፋቸውና በማሸነፋቸው ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
በሙሉ ግርማይ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: