Search

እርቅ፣ ሰላም፣ ፍቅር እና አብሮነት የሚጠናከሩበት የ‘ድሽታግና’ በዓል

እሑድ ኅዳር 20, 2019 88

"ድሽታግና የሰላም ምንጭ፣ የአብሮነት ቅርስ፣ የልማት መሠረት" በሚል መሪ ሐሳብ የአሪ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል፣ በአዲስ አበባ የኦሮሞ ጥናትና ምርምር ማዕከል አዳራሽ በድምቀት እየተከበረ ነው።

ድሽታግና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በአሪ ዞን እንዲሁም የብሔረሰቡ ተወላጆችና ወዳጆች በሚገኙባቸው የተለያዩ አካባቢዎች የሚከበር የዘመን መለወጫ በዓል ነው።

በዓሉ በባህሪው የማኅበረሰቡን አንድነት የሚያጠናክር እና የቆዩ ባህላዊ እሴቶችን የሚያንጸባርቅ ነው።

በበዓሉ ወቅት ከሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል ምስጋና ማቅረብ፣ የተጣሉትን ማስታረቅ፣ የተቸገሩትን መርዳት እንዲሁም ፍቅርና አብሮነትን ማጠናከር ይገኙበታል።

እነዚህ እሴቶች የማኅበረሰቡን ማኅበራዊ ትሥሥር ከማጠናከር ባለፈ ለሰላም ግንባታ ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ሀገራዊ ቅርሶች ናቸው።

በአዲስ አበባ የኦሮሞ ጥናትና ምርምር ማዕከል እየተከበረ የሚገኘው የድሽታግና በዓል፣ በሀገራችን ጥላቻና ግጭት ተወግዶ ሰላም፣ ፍቅር፣ ወንድማማችነት እና መረዳዳት እንዲጎለብት የላቀ አስተዋጽኦ  እያበረከተ ይገኛል ተብሏል።

የአሪ ዞን አስተዳደር የዘንድሮውን የድሽታግና በዓል በማዕከሉ አዳራሽ እያከበረ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ የበዓሉ ባህላዊ እሴቶች በስፋት እንዲታወቁና በሌሎች አካባቢዎችም እንዲተገበሩ ጥሪ ቀርቧል።

በዓሉ የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶችን በማስረጽ ለዘላቂ ሰላምና ለልማት መሠረት የሚጥል መሆኑም ተመላክቷል።

በመሐመድ ፊጣሞ

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: