Search

ከ1 ሺህ በላይ ስፖርተኞች የሚሳተፉበት የባህል ስፖርቶች ውድድር እና ፌስቲቫል በሻሸመኔ

እሑድ ኅዳር 20, 2019 74

በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የሚካሂደው 32ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 19ኛው የባህል ፌስቲቫል በሻሸመኔ ከተማ በድምቀት መካሄድ ጀምሯል።

‎ፌስቲቫሉ የኢትዮጵያን ባህላዊ እሴቶች፣ ትውፊቶችና ታሪካዊ ሀብቶች በማስጠበቅና ለትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ወሳኝ ሚና እንዳለውና የተለያዩ ማኅበረሰቦችን  በአንድ መድረክ በማሰባሰብ ማኅበራዊ ትሥሥርን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል።

‎ለስምንት ቀናት በሚቆየው ፌስቲቫል በ10 የተለያዩ የባህል ስፖርት ዘርፎች ውድድሮች የሚካሄዱ ሲሆን፣ ከ1 ሺህ በላይ ስፖርተኞች በውድድሩ ይሳተፋሉ።

‎በፌስቲቫሉ ላይ ‎የተለያዩ ባህላዊ ውዝዋዜዎች፣ የባህል አልባሳት እና ባህላዊ ምግቦች ለዕይታ እንደሚቀርቡ ተመላክቷል።

‎የባህል ልውውጥ፣ የወንድማማችነት፣ የመተዋወቅና የጋራ እሴቶችን የማጎልበት የአንድነት መድረክ መሆኑም ነው የተገለጸው።

‎በሚካኤል ገዙ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: