የአሪ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል በሆነው “ድሽታግና” የመደመር እሴቶችን አቅፎ የያዘ ጠንካራ በዓል መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ነቢዩ ባዬ ገለጹ።
ሚኒስትር ዴኤታው በአዲስ አበባ የኦሮሞ ጥናትና ምርምር ማዕከል በተከበረው የ“ድሽታግና” በዓል ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ የመደመር መንግሥት መሠረታዊ እሳቤ ከሀገር በቀል እሴቶች ጋር ያለውን ጥልቅ ተዛምዶ አመላክተዋል።
የድሽታግና ዋነኛ እሴቶች የሆኑት ተካፍሎ መብላት፣ በፍቅር መኖር እና መረዳዳት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበዓላት ወቅት ከአቅመ ደካሞች ጋር ማዕድ የመቋደስ ልምድ ጋር በቀጥታ የሚናበቡ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ምስጋናን፣ ጽዳትንና ውበትን እንደ ወሳኝ እሴቶች አንስተው፣ ፈጣሪንና ሰዎችን የማመስገን ባህል የድሽታግና መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል።
በአዲስ ዓመት መባቻ ቤትን፣ አካባቢንና ራስን ይቅርታ ማለት እንዲሁም የአንዱ ብርታት የሌላውን ድካም የሚሞላበት ሂደት የብሔረሰቡ የመረዳዳት እሳቤ መሆኑን አብራርተዋል።
ኢትዮጵያውያን የድሽታግናን የትብብር እሴቶች በመያዝ ሀገርን ታላቅ ለማድረግ እንዲነሱ ጥሪ አቅርበዋል።
በመሐመድ ፊጣሞ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: