Search

የተሰሩት የኮሪደር ልማቶች ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ታሳቢ ያደረጉ ናቸው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሓሙስ ነሐሴ 29, 2017 53

በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩት የኮሪደር ልማት ስራዎች ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረገ ናቸው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

በዛሬው ዕለት 5ኛው ከመስቀል አደባባይ - መገናኛ - ሳውዝጌት ያለው የ8 ኪ.ሜ ኮሪደር ልማት ተመርቋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት፤ የተሰሩት የኮሪደር ልማቶች ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ታሳቢ ያደረጉ ናቸው ብለዋል፡፡

ዛሬ በተመረቀው የኮሪደር ልማት የባቡር መንገዱን ጨምሮ በአካባቢው ያሉ በርካታ ህንፃዎች ወደ መንገድ ጠጋ ብለው መስራታቸው እና አንዳንድ ከዚህ ቀደም የተገነቡ ግንባታዎች ምቹ አለመሆናቸው አስቸጋሪ ነበር ያሉት ከንቲባዋ፤ ሆኖም ግን ችግሮችን ተቋቁሙ ጥሩ ስራ መስራት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ይህ የኮሪደር ልማት የተለያዩ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የልጆች የመጫወቻ ቦታዎች፣ የስፖርት ሜዳዎች በውስጡ የያዘ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረጉ ናቸውም ብለዋል ከንቲባዋ፡፡

በዋናነት ትኩረት የምንሰጠው ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፤ አዲስ አበባ በኮሪደር ልማቱ ለህዝብ ስፍራ ያላት፣ ለጋራ መገልገያ ቦታዎች የምትሰጥ እና ኢንቨስት የምታደርግ ከተማ መሆኗን ያሳየንበትም ነው ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ሁል ጊዜ ህዝባችንን ለማገልገል ያለእረፍት እንሰራለን ያሉት ከንቲባዋ፤ እነዚህ ልማቶች የተሰሩት ከከተማዋ ማህበረሰብ ጋር በመሆኑ ለዚህም ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው ብለዋል፡፡

በሐይማኖት ከበደ

#ebcdotstream #EBC #addisababa #corridordevelopment