Search

ኢትዮጵያ - አዲሷ የአፍሪካ የኢንቨስትመንት ማዕከል

ሓሙስ የካቲት 19, 2018 58

ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን (FDI) በመሳብ ሁለተኛ ደረጃ መያዝ መቻሏን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል።

ይህ ታላቅ ስኬት የተመዘገበው 2016 . የተጀመረውን ታሪካዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ተከትሎ ባለሀብቶች በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ምኅዳር ላይ ያላቸው እምነት በማደጉ ነው።

በኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አራጌ ክብረት እንደገለጹት፤ 2017 በጀት ዓመት 4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ካፒታል መሳብ ተችሏል።

በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ደግሞ 245 አዳዲስ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል። በዓመቱ መጨረሻ 5.17 ቢሊዮን ዶላር ለማስገኘት የታቀደው ግብ አፈጻጸምም አበረታች ደረጃ ላይ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንድትሆን ካደረጓት ምክንያቶች መካከል ሥልታዊ አቀማመጧ፣ ሰፊ እና ታታሪ የሰው ኃይል፣ ምቹ የአየር ንብረት እና ተፈጥሯዊ ጸጋዎቿ ተጠቃሽ ናቸው።

እንደ ቶዮ (Toyo) ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች በፀሐይ ኃይል ዘርፍ መሰማራታቸው ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ትልቅ አቅም መፍጠሩን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማጠናከር እና አሠራሩን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ በማድረግ ባለሀብቶች ያለ እንግልት በፈጣን መንገድ እንዲስተናገዱ እየሠራ ይገኛል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የውጭ ምንዛሪ በገበያ እንዲመራ መደረጉ፣ የመሠረተ ልማት መስፋፋት እና የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ለታዳሽ ኃይል አቅርቦት ያለው ሚና የዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን ፍላጎት በእጅጉ ጨምሮታል።

በላሉ ኢታላ

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #EconomicReform #InvestInEthiopia