የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ክሪፕቶ ከረንሲን ጨምሮ ፈቃድ በሌላቸው የተለያዩ መተግበሪያዎች የሚከናወኑ የአቻ ለአቻ (P2P) የዲጂታል ግብይቶችን በጊዜያዊነት ማገዱን አስታወቀ።
ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ፣ ግለሰቦች ከባንኩ እውቅና በሌላቸው መተግበሪያዎች ግብይት እየፈጸሙ መሆኑ በክትትል እንደደረሰበት ጠቅሷል።
እነዚህ መደበኛ ያልሆኑ ግብይቶች የገበያ መረጋጋትን ከማናጋት ባለፈ፣ ለሳይበር ወንጀል፣ ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ለፋይናንስ ሽብርተኝነት የተጋለጡ መሆናቸውን ባንኩ አብራርቷል።
በተጨማሪም የውጭ ምንዛሪ ዋጋን የማሳሳትና የግብይት ግልጽነት ችግሮችን እንደሚያስከትሉ ገልጿል።
ባንኩ የዲጂታል ግብይት ቴክኖሎጂዎችን ደህንነት የሚያረጋግጥ አጠቃላይ የቁጥጥር ማዕቀፍ በመዘርጋት ላይ መሆኑን ጠቁሞ፣ ይህ ማዕቀፍ ይፋ እስኪሆን ድረስ ማንኛውም ፈቃድ የሌለው የዲጂታል ግብይት የተከለከለ መሆኑን አሳስቧል።
የፋይናንስ ሥርዓቱን ታማኝነት ለመጠበቅም ከዓለም አቀፍ ተቆጣጣሪዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እየተደረገ መሆኑንም ባንኩ አመልክቷል።
#Ebc #Ethiopia #NationalBankOfEthiopia #DigitalCurrency #FinancialSecurity