ኢትዮጵያ እና ኢስዋቲኒ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ለስኳር የሚሆን የሸንኮራ አገዳ ልማት ላይ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መድረሳቸውን የግብርና ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ ገልጸዋል፡፡
የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ራስል ሚሶ ዲላሚኒ ከግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ ጋር በመሆን፣ በጅማ ዞን የቡና ልማት ሥራዎችን እንዲሁም በጅማ ከተማ የኮሪደር ልማትን እና የአባ ጅፋር ቤተ-መንግስትን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ራስል ሚሶ ዲላሚኒ በጅማ ዞን ከሚገኙ ለዓለም ገበያ ቡናን ከሚያቀርብ አምራች አርሶአደሮች ጋር መወያየታቸው ተገልጿል።
በዚህም ከኢትዮጵያ የቡና ልማት እና ከሌሎች የግብርና ልማት ሥራዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልምድ መውሰዳቸው ተጠቅሷል፡፡
የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ሁለቱ ሀገራት በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በሸንኮራ አገዳ ልማት በጋራ ለመስራት ከመግባባት ደርሰዋል።