ከ70ሺ በላይ ሰራተኞችን የሚያስተዳድረው ሚድሮክ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተቋሙን የቤተሰብ ቀን እያከበረ ነው።
ሚድሮክ ኢንቨሶትመንት ግሩፕ ካለፈው በጀት ዓመት ትርፉ በ134 በመቶ ማሳደጉን አስታውቆ፤ ለዚህ ውጤት አስተዋፆ ላበረከቱ 588 ሰራተኞቹ ከ100ሺ ብር ጀምሮ አስከ 500ሺ ብር ሽልማት አበርክቷል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተቋሙ ዓመታዊ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የእቅድ ሪፖርት ኮርፖሬት ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ሙሉጌታ ተቋሙ ባሳለፈው በጀት ዓመት ከሁሉም ዘርፎች የተሻለ አፈጻጸም አስመዝግቧል ብለዋል።
በተለይም የሚድሮክ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከታቀደው በላይ 102 በመቶ ሲያከናውን፣ የማዕድን ዘርፉ ደግሞ ከታቀደው 51 በመቶ ማከናወኑ ተመላክቷል። ይህም ከምርት ብዛት ይልቅ በዋጋ ላይ በተፈጠሩ ማስተካከያዎች የተነሳ የተገኘ አፈፃፀም እንደሆነ ገልጸዋል።
ሚድሮክ በቀጣይ ዓመትም ምርታማነትን እና ትርፋማነቱን ለማሳደግ አዳዲስ ቴክኖሎጂ እና የአሰራር ዘይቤን እንደሚጠቀም ተመላክቷል።

በተለይ ብክነትን በመቀነስ የውስጥ አቅምን ማጠናከር እና የገበያ አማራጮችን ማስፋት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ተብሏል።
ሚድሮክ በበጀት ዓመቱ ብቻ 1.1 ቢሊዮን ብር ለማኅበራዊ አገልግሎት ወጪ ማድረጉ ተጠቁሟል።
ይህም ለምገባ ማዕከላት፤ ለኩላሊት እጥበት ማሽን ግዢ እና ሌሎች ማኅበራዊ ሃላፊነቶችን ለመወጣት የዋለ መሆኑ ተገልጿል።
በኤዶም አማረ