የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2026 ባለአራት ኮከብ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ በመባል ከመንገደኞች ተሞክሮ ማሕበር (Airline Passenger Experience Association APEX) ዕውቅና ተሰጥቶታል።
ዕውቅናው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአገልግሎት፣ በፈጠራ እና በተሳፋሪ ተሞክሮ የላቀ ብቃት ካላቸው ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች መካከል የሚመደብ መሆኑን ያረጋገጠ መሆኑን አየር መንገዱ አመላክቷል።