ከ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ተፈታኞች ጋር ሲነፃፀር ዘንድሮ ከ12 ሺ 500 በላይ ተጨማሪ ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ ውጤት አምጥተው አልፈዋል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።
በ2017 ዓ.ም ከተፈተኑት ውስጥ 48 ሺ 929 ተማሪዎች ማለፋቸውን አስታውቀው፤ በ2016 ዓ.ም ግን ያለፉት ተማሪዎች 36 ሺ 409 ብቻ እንደነበሩ አስታውሰዋል።
ዘንድሮ ካለፉት ተማሪዎች ውስጥ 18 ሺ 478ቱ ሴቶች መሆናቸውንም የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልፀዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ