Search

የምንመኛትን አፍሪካ ዕውን የምናደርግበት አጀንዳ 2063

ሓሙስ የካቲት 05, 2018 99

አጀንዳ 2063 የአፍሪካ ኅብረት በተመሠረተ 50 ዓመቱ ማለትም .. 2013 የፀደቀ ሲሆን አህጉሪቱን 50 ዓመታት ውስጥ ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ የታለመ ስትራቴጂካዊ ፍኖተ ካርታ ነው።

"የምንመኛት አፍሪካ" በሚል መሪ ቃል የሚመራው ይህ ራዕይ፣ አፍሪካን በራሷ ልጆች አቅም የምትመራ፣ ሰላማዊ እና በዓለም መድረክ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንድትሆን ያለመ ነው።

2014 እስከ 2023 የነበረው የመጀመሪያው ዐሥርት ዓመት ትኩረቱ የሕግ ማዕቀፎችን መዘርጋት እና አህጉራዊ ተቋማትን ማጠናከር ላይ ነበር።

አሁን 2026 የምንገኝበት "ሁለተኛው የዐሥርት ዓመት የትግበራ ዕቅድ" (2024 - 2033) ደግሞ "የማፋጠኛ ምዕራፍ" ተብሎ ይታወቃል።

በዚህ ወቅት ትኩረቱ ረቂቅ ሕጎችን ወደ ተጨባጭ የልማት ውጤቶች መቀየር ነው።

በአጀንዳ 2063 እስካሁን ምን ተሳካ? 

የአጀንዳው ዋነኛ ስኬት ተደርጎ የሚወሰደው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) አተገባበር ነው።

በዚህ የፈረንጆቹ 2026 መጀመሪያ ላይ እንደ ናይጄሪያ ያሉ ግዙፍ ኢኮኖሚዎች የንግድ እንቅፋቶችን በማንሣታቸው አህጉራዊ ትሥሥሩ እየጠነከረ መጥቷል።

በተለይም በሀገር ውስጥ ገንዘቦች ግብይት እንዲፈጸም የሚያስችለው የፓን አፍርካ የክፍያ እና የስሌት ሥርዓት (Pan-African Payment and Settlement System /‘PAPSS’/) የተባለው የክፍያ ሥርዓት፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ነጋዴዎች ያለዶላር እጥረት ድንበር ተሻጋሪ ንግድ እንዲያካሂዱ በር ከፍቷል።

አጀንዳ 2063 የረጅም ጊዜ ጉዞ ቢሆንም፣ 2026 የታዩት የንግድ እና የቴክኖሎጂ እንቅስቃሴዎች አህጉሪቱ በትክክለኛ መንገድ ላይ መሆኗን ያሳያሉ።

በአንፃሩ በተለያዩ የአህጉሪቱ ክፍሎች የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች "የተኩስ ድምፅ የማይሰማባት አፍሪካ" የሚለው ግብ እንዳይሳካ አግደዋል።

በአጠቃላይ፣ የአፍሪካ መንግሥታት ከፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ባለፈ የግሉን ዘርፍ እና ወጣቱን ኃይል በንቃት ካሳተፉ፣ የምንመኛት አፍሪካ ዕውን መሆኗ አይቀሬ ነው።

 

በዮናስ በድሉ