ለመንገደኞች፣ ለአውሮፕላን አብራሪዎችና ለበረራ አስተናጋጆች እንዲሁም ለአውሮፕላኖች ደኅንነት ሲባል በበረራ ወቅት ፓወር ባንክን ጨምሮ የሊቲየም-አዮን ባትሪ ያላቸውን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን መጠቀም የተከለከለ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።
በጉዞ ወቅት የሊቲየም-አዮን ባትሪ ያላቸው ማናቸውም የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች አውሮፕላኑ ውስጥ ከተሳፋሪው አናት በላይ በሚገኙ የዕቃ ማስቀመጫዎች ውስጥም መቀመጥ እንደሌለባቸው እና ከተሳፋሪው መቀመጫ ሥር ሊቀመጡ እንደሚገባ ተመላክቷል።
የአየር መንገዱ የሊቲየም ባትሪ ያላቸውን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በተመለከት ግልፅ የደኅነት ጥበቃ ሕጎችን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

በላሉ ኢታላ