ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድን ተቀብለው በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።
"ውይይታችን በዐበይት ዘርፎች ለረዥም ዘመናት የዘለቀውን የሁለቱ ሀገሮቻችንን ትስስር በማስፋት እና የወል ፍላጎቶቻችን በሆኑ ቀጣናዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ትብብራችንን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት።
#Ethiopia #SaudiArabia #diplomacy #AbiyAhmed #EthiopianBroadcastingCorporation #EB