አሜሪካ እና ቻይና የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ የሆነው ቲክቶክ በአሜሪካ ውስጥ የሚቀጥልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የማዕቀፍ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ለመጪው ዐርብ ቀጠሮ ይዘዋል።
ሀገራቱ የቲክቶክን ባለቤትነት እና ቁጥጥር አሜሪካ በምትጋራበት ሁኔታ ላይ በስፔን ማድሪድ ውይይት ላይ የነበሩ ሲሆን፤ ይህንኑ ለማመቻቸት የሚያስችል የማዕቀፍ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የአሜሪካ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
የአሜሪካ የግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቢንሴንት እንደገለጹት፥ አሜሪካ ስምምነት ላይ ካልተደረሰ ቲክቶክን እስከ መጪው ረቡዕ ልታግደው መወሰኗ ቻይናውያን ተደራዳሪዎች ስምምነት ላይ እንዲደርሱ አስገድዷቸዋል።
በማዕቀፉ መሠረት ስምምነቱን ለማጠናቀቅ ቲክቶክ ሳይታገድ የሚቆይበት ጊዜ ለ90 ቀናት ሊራዘም እንደሚችል ቢንሴንት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
በለሚ ታደሰ
#EBC #ebcdotstream #tiktok