የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ሆቴሎች በ2025 የመጀመሪያ አጋማሽ 16.1 ሚሊዮን እንግዶችን አስተናግደዋል::
የኢኮኖሚና ቱሪዝም ሚኒስትሩ አቶ አብዱላህ ቢን ቱቅ አል ማርሪ እንደገለጹት፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ የሆቴል ዘርፍ በ2025 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ከ16.1 ሚሊዮን በላይ እንግዶችን ተቀብሏል።
ይህ ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ5.5 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።
በሦስተኛው የሆቴል ዘርፍ አማካሪ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትሩ፣ ይህ ስኬት የተገኘው የአገሪቱ አመራር እና የመንግሥትና የግል ተቋማት በትብብር በመሥራታቸው ነው ብለዋል።
በተጨማሪም፣ ይህ ውጤት ዩኤኢ እንደ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ማዕከል ያላትን ተወዳዳሪነት ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል።
የእንግዶች አማካይ ቆይታም ወደ 3.5 ምሽት ከፍ ብሏል።
በአሁኑ ጊዜ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ከ216,000 በላይ ክፍሎች ያሏቸው 1,243 የሆቴል ተቋማት አሏት።
በሰለሞን ገዳ