በአፋር ክልል ፋንቲ ረሱ ኡዋ ወረዳ በመስኖ እና በክረምት ዝናብ ከ3 ሺ 400 ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ የግብርና ልማት እየተከናወነ ይገኛል።
የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ማንጎ ፣ ፓፓዬ ፣ ሙዝ እንዲሁም በቆሎ በመስኖ እየለማ እንደሚገኝ የወረዳው አስተዳደር አቶ መሃመድ ሚኢዬ ለኢቲቪ ገልፀዋል።

የክረምት ወቅት ዘግይቶ የጀመረ ቢሆንም የዝናብ መጠኑ አሁን ባለው ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ጥሩ ምርት ለመሰብሰብ ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል።
በኡዋ ወረዳ የግብርና ልማቱ እየተከናወነ የሚገኘው በአብርቶ አደሮች እና ከፊል አርሶ አደሮች ማሳ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
የኡዋ ወረዳ በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ከፍተኛ ፈተናዎች ሲደርስበት እንደነበርም አቶ መሃመድ አስታውሰዋል።
አሁን ላይ ኅብረተሰቡ ጫናዎችን ተቋቁሞ ራሱን በምግብ እንዲችል በግብርናው ዘርፍ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።
በሁሴን መሀመድ