Search

የምንደመረው በአንድ ጭንቅላት ለማሰብ ሳይሆን ለአንድ ሀገር ለማሰብ ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ረቡዕ መስከረም 07, 2018 35

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር  እሳቤ ዙሪያ አራተኛ መጽሐፋቸውን አስመርቀዋል።

የመደመር መንግሥት የተሰኘው መጽሐፋቸው በቀደሙት የመደመር መፃሕፍት የተቀመጡ ነጥቦች ወደ መንግሥታዊ ወይም ተቋማዊ ፍኖት የሚመጡበትን ዓውድ የሚያትት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ፥ ኢትዮጵያ ለሁላችንም ትበቃለች፤ የምንደመረው በአንድ ጭንቅላት ለማሰብ ሳይሆን ለአንድ ሀገር ለማሰብ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የአቅም እና የአቋም ድምር ካለ ኢትዮጵያውያን የማይሻገሩት ፈተና የለም፤ የምትመስል ሳይሆን የምትመሰል ሀገር ነው መገንባት የምንፈልገው ነው ያሉት።

በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር 48 ቢሊዮን ችግኝ መትከል መቻል ቀዳሚው ትዕምርት መሆኑን አንስተዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በትውልድ መካከል ሳይቆም ፈተናዎችን ተሻግሮ እውን የሆነው ፕሮጀክት መሆኑን አንስተዋል።

በራስ አቅም፣ በራስ ገንዘብ ከጭለማ ልምምድ ነፃ የወጣ ከተማ ግንባታ አካል የሆነው የኮሪደር ልማትም ሌላኛው  ተምሳሌት ነው ብለዋል።

የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የስንዴ ልማትም በተመሳሳይ ኢትዮጵያን ተምሳሌት የሚያደርጓት ሥራዎች እንደሆኑ ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ  የይቻላል እሳቤን ለሌሎች ሀገራት የማስተጋባት አቅም አላት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ከተደመርን፣ በጋራ ለመስራት ከወሰንን እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል።

በታሪክ ካየነው ስብራት ተምረን ወደ ምንፈልገው ራዕይ መድረስ አለብን ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቀጣዩ መጽሐፋቸው የመደመር ስሌት በፍሪሊዮን በሚል ርዕስ ለንባብ እንደሚበቃ ጠቁመዋል።

በቤተልሔም ገረመው

#EBCdotstream #YemedemerMengist #PMAbiyAhmed

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: