እኛ መደመር ስንል ጠላቶቻችን ይደነግጣሉ፤ ምክንያቱም ስንደመር እንዴት ታሪክ እንደምንሠራ ከጥንት ጀምሮ አሳይተናቸዋልና ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፍ ምረቃ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት።
ኢትዮጵያውያን በዘር ሳንከፋፈል በጋራ ስንቆም መፍጠር፣ መፍጠን፣ አስፈላጊ ሲሆንም መዝለል እንችላለን ብለዋል።
መከፋፈል የኢትዮጵያውያን ሀሳብ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የምንሰማውን ሀሳብ ለመመርመር ካልተዘጋጀን ከተቀባይነት እና ከተከታይነት በመላቀቅ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ ከባድ እንደሚሆን አመላክተዋል።
በመደመር፣ የመነጣጠል ሀሳብን በመከላከል አንድ መሆን እንደሚቻል አብራርተዋል።
ኢትዮጵያውያን የአንችልም ሀሳብን ከውስጣችን በማስወገድ፣ እንችላለን በማለት፣ በጠራ እሳቤ ከግል ፍላጎት ባሻገር ለጋራ ፍላጎት መትጋት አለብን ሲሉ አሳስበዋል።
የመደመር መንግሥት የእንችላለን እሳቤን የሚያጠናክሩ እቅዶችን ያመላከተ፤ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥም በትክክለኛ መስመር ላይ ያለ ስለመሆኑ ገልጸዋል።
በቢታንያ ሲሳይ
#EBCdotstream #YemedemerMengist #PMAbiyAhmed