Search

የመደመር መንግሥት ጊዜ ካለፈ በኋላ ትውልድ ይፋረደኝ የሚል አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ረቡዕ መስከረም 07, 2018 37

የመደመር መንግሥት ጊዜ ካለፈ በኋላ "እንዲህ አስቤ ነበር"ብሎ ትውልድ ይፋረደኝ የሚል ሳይሆን በተሰጠው ጊዜ የሚገባውን ታሪክ ሠርቶ ለማለፍ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
መጽሐፉ የተዘጋጀው ጊዜ ካለፈ በኋላ "አላሠራ አሉኝ እንጂ፣ እንዲህ ለመሥራት አስቤ ነበር" የሚለውን ምክንያት ለማስቀረት እንደሆነ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡
የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ ለምን ደሃ ሆነች? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ እያንዳንዱን የመጣንበትን መንገድ መርምሮ ዛሬ ለመፍትሔ የሚሠራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ ማሳበብ ሳይሆን በተሰጠ ጊዜ ተጠቅሞ ታሪክን ሠርቶ ለትውልድ ማስተላለፍ ወሳኝ ስለሆነ መጽሐፉ ይህን መንገድ ለማሳየት ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡
በለሚ ታደሰ